በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

ቅድሚያ ስለመስጠት


የምታዩት ቢጫ ሚኒባስ ድርጊት በጣም ይገርማል። ከቆመበት አንደኛው ጥግ ተነስቶ ወደ ሌላኛው ጥግ መንገድ እያቋረጠ ነው።

የቪዲዮ መጀመሪያ ላይ እንደመጣሁ መዞር የምችል ቢመስልም ዕይታዬ በተቃራኒ አቅጣጫ መጥቶ እየዞረ በሚገኘው ተሽከርካሪ የተገደበ ነው፡፡

በዚህ ቪዲዮ የምትመለከቱት አሽከርካሪ እንደመጣ ዘው ብሎ የመንገድ መጋጠሚያውን ለማቋረጥ መሞከር አልነበረበትም።

ከፓርኪንግ ስንነሳ በትራፊክ ፍሰት ውስጥ በቂ ክፍተት እስኪፈጠር ድረስ ከፓርኪንግ ረድፍ በከፊልም መውጣት የለብንም፡፡

ይህ የምታዩት ተሽከርካሪ ፍሬቻ ሳያበራ፣ ከቆመበት ተነስቶ፣ የትራፊክ ፍሰቱን እያስተጓጎለ፣ ወደ መንገድ ተቀላቅሏል።