በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

ጠንቃቃ የምሽት አነዳድ

በዚህ ምሳሌ ላይ እንደሚታየው አሽከርካሪው በደረቅ መንገድ በ40 ኪሜ/ሰዓት እየተጓዘ ሲሆን ድንገት ለመቆም የሚያስፈልገው ርቀት ወደ 16 ሜትር (የ4.5 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  እንደሚሆን አይተናል። ዕይታው ደግሞ ወደ 20 ሜትር (የ5.5 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ነው። ታዲያ ድንገት የአደጋ ሁኔታ ቢከሰት የአደጋውን መንሰዔ የሚያየው 20 ሜትር (የ5.5 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ርቀት ላይ ሲሆን ለመቆም ደግሞ ወደ 16 ሜትር (የ4.5 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ነው የሚያስፈልግው። በዚህ ሁኔታ አደጋውን ለማስቀረት ከፍተኛ ዕድል አለው ማለት ነው።

 

ይህን በማወቃችን ምን ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን?

በማንኛውም ወቅት ስናሽከረክር (በቀንም ይሁን በምሽት) የሚቀጥሉትን 2 ጥያቄዎች ለራሳችን መጠየቅ ግድ ይላል። የመጀመሪያው ጥያቄ - አሁን በያዝኩት ፍጥነት የአደጋ መንሰዔ ቢከሰት ድንገት ለመቆም ምን ያህል ርቀት ያስፈልገኛል? - የሚለው ሲሆን ካገኘነው መልስ በመነሳት ቀጣዩ ጥያቄ ደግሞ - ያን ያህል ርቀት በግልጽ ማየት እችላለሁ ወይ? - የሚለው ነው። ከላይ በምሳሌ ከጠቀስነው ሁኔታ በመነሳት መልሱ - አዎ፣ ይታየኛል - በመሆኑ አደጋው የመከሰቱ እድል እጅጉን የቀነሰ ነው። ፍጥነታችንን ከዕይታችን ጋር የተጣጣመ ነው ማለት ነው።
ማሳሰቢያ
  • በአገራችን በሚገኙ በቂ መብራት በሌላቸው መንገዶች፣ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጡ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በምሽት ስናሽከረክር እይታችን በጣም የተገደብ መሆኑን - ምናልባትም 20 ሜትርም (የ5.5 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ላይደርስ እንደሚችል - መገንዘብ ያስፈልጋል።
  • የዕይታ መገደብን ለማሳየት በዚህ ገጽ ላይ የምሽት አነዳድን እንደምሳሌ ተጠቀምን እንጂ፣ በቀንም ቢሆን የመንገዱ አቀማመጥ፣ የሌሎች ተሽከርካሪዎች መኖር ወዘተ... እይታችን እጅጉን የተገደበ እንዲሆን ሊያደርጉ ይችላሉ።