በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

በእያንዳንዷ ሰከንድ የምንጓዘውን ርቀት እንደሚከተለው ማስላት እንችላለን

የፍጥነታችንን የ10 ቤት ቁጥር በ 3 በማባዛት በእያንዳንዷ ሰከንድ የምንሸፍነውን ርቀት መተንበይ እንችላለን። ለምሳሌ በተንቀሳቃሽ ሰዕሉ ላይ የሚታየው ተሽከርካሪ በ 50 ኪሜ/ሰዓት እየተጓዘ ሲሆን፣ የፍጥነቱን የ10 ቤት ቁጥር ፣ ማለትም 5 ን በ 3 በማባዛት (5 x 3) ወደ 15 ሜትር (የ 4 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  በእያንዳንዷ ሰከንድ እንደሚሸፍን ማወቅ ይችላል። በሌላ አገላለጽ 4 ቪትዝ መኪናዎች ቢደረደሩ የሚሰጡትን ርቀት የሚጠጋ ማለት ነው።

በ 60 ኪሜ/ሰዓት እየተጓዘ ቢሆን 6 ን በ 3 በማባዛት (6 x 3) ወደ 18 ሜትር (የ 5 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  በእያንዳንዷ ሰከንድ ይሸፍናል ማለት ነው።

 

ይህን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?

የአደጋ መንስኤ ሲከሰት አብዛኛውን ጊዜ ቢያንስ የ 1 ሰከንድ የምላሽ ጊዜ (ፍሬን መርገጥ እስክንጀምር) ይወስድብናል ተብሎ ይታመናል። ይህ ማለት በ 50 ኪሜትር/ሰዓት እየተጓዝን የአደጋ መንስኤ ቢከሰት የፍሬን ፔዳላችንን መርገጥ ሳንጀምር ወደ 15 ሜትር (የ 4 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  እንጓዛለን ፤ የ 2 ሰከንድ የምላሽ ጊዜ ቢወስድብን ወደ 30 ሜትር (የ 8 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  የሚጠጋ ርቀት ፍሬን ሳንረግጥ እንጓዛለን። ከዚያ በኋላ ደግሞ ፍሬን ረግጠን የምንጓዘው ተጨማሪ ርቀት መኖሩን ማስተዋል ይገባል።

 

ይህን በማወቃችን ምን ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን?

በሌሎች ገፆች ላይ በዝርዝር እንደምንመለከተው የምንገኝበትን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በቂ ርቀት መጠበቅና ፍጥነታችንን መገደብ እንደሚገባን እንገነዘባለን።