በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

ከሌሎች ጋር ስለማሽከርከር

  • በአንድ ጊዜ በአንድ የመንገድ ረድፍ ውስጥ ብቻ ተወስኜ አሽከረክራለሁ። በከፊል አንዱን ርድፍ፣ በከፊል ደግሞ ሌላኛውን ረድፍ ይዞ ማሽከርከር ትክክል አይደለም፤
  • የቀኙን ረድፍ ይዤ የግራውን ረድፍ ለፈጣን ተሽከርካሪዎች ክፍት አደርጋለሁ፤
  • ከፊቴ ከሚገኘው ተሽከርካሪ ጋር በቂ እርቀት እጠብቃለሁ፤
  • በየጊዜው፣ ግን ለአፍታ፤ በውስጥ እና በውጪ መስታወቶች እመለከታለሁ። ይህም በዙሪያዬ ስላለው ሁኔታ ግንዛቤ ስለሚሰጠኝ ድንገተኛ እና አደገኛ እንቅስቃሴ እንዳላደርግ ያግዘኛል።