በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

ከሌሎች ጋር ስለማሽከርከር


መንገድ የግላችን እና ብቻችንን እንዳሻን የምንሆንበት ሳይሆን ከሌሎች ጋር በጋራ የምንገለገልበት መሠረተ ልማት ነው፡፡ ለዚህም የተቀመጡ የትራፊክ ህጎችን ማወቅ፣ ማክበርና በቀናነት መተግበር ይጠበቅብናል፡፡

በጥሩ የዕይታ ሁኔታ፣ ከፊታችን የሚገኘውን ተሽከርካሪ ቢያንስ የ2 ሰከንድ ርቀት ጠብቀን እንድንከተል ይመከራል። በመጥፎ የዕይታ/የመንገድ ሁኔታ (ዝናብ፤ ጭለማ) ይህን የመከተያ እርቀት ወደ 4 ሰከንድ ማሳደግ ይመከራል።

ብዙ ጊዜ 200 እና 300 ሜትር ተጉዘን መዞር ሲገባን ፣ አቋራጭ ፍለጋ ህግ በመተላለፍ በተቃራኒ አቅጣጫ ስንጓዝ ይስተዋላል፡፡

ይህ አደጋ በትክክል እንዴት እንደደረሰ ለመናገር ቢያስቸግርም አንዳንድ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ሃሳቦችን ግን መሰንዘር ይቻላል፡፡