በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

ከፓርኪንግ ረድፍ ስለመነሳት

ከፓርኪንግ መቆሚያ ለመውጣትና የቀኙ ረድፍ ውስጥ ገብቶ የትራፊክ ፍሰቱን በደህንነት ለመቀላቀል የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅብኛል

  • ከፓርኪንግ ረድፍ ለስንዝርም ሳልወጣ አላፊ መኪናዎችን ቅድሚያ እየሰጠሁ አሳልፋለሁ፡፡ አስፈላጊ ከሆነም እዚያው ረድፍ ውስጥ ወደፊት ወደኋላ እያልኩ ከፊቴ የቆመ መኪና ካለ ሳልነካው የምወጣበትን ሁኔታ አመቻቻለሁ፡፡
  • በትራፊክ ፍሰቱ ውስጥ በቂ ክፍተት ሲፈጠር ብቻ ከቆምኩበት በመንቀሳቀስ ጉዞ እጀምራለሁ፡፡

ብዙ ጊዜ በከተማችን የሚስተዋለው አሽከርካሪዎች የመኪናቸውን አፍንጫ አስወጥተው የቀኙን ረድፍ የትራፊክ ፍሰት ካስተጓጎሉ በኋላ አላፊ መኪና ስለመኖሩ ለማየት ይሞክራሉ፡፡ ይህ ለአደጋ የሚያጋልጥ አደገኛ እንቅስቃሴ ነው፡፡