በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

ቅድሚያ መከልከል - ምሳሌ 1

የምታዩት ቢጫ ሚኒባስ ድርጊት በጣም ይገርማል። ከቆመበት አንደኛው ጥግ ተነስቶ ወደ ሌላኛው ጥግ መንገድ ሲያቋርጥ ለአላፊ መኪናዎች ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት ብዙም ግድ የሚለው አይመስልም። እንዲያውም ጥሩምባ ሲደረግለት "ምንድን ነው የምትሉኝ? ለምን ትረብሹኛላችሁ? ዝም ብላችሁ አታልፉም ወይ፣ ማን ከለከላችሁ" የሚል ይመስላል። በዚህ ድርጊቱ እንቅስቃሴዬን አስተጓጉሎ እንድቆም ስላስገደደኝ ቅድሚያ እየከለከልኝ ነው።

የትንሿ ቪትዝ አሽከርካሪ ደግሞ ቅድሚያ እንደሚሰጥ የሚገነዘብ ይማስላል። ሆኖም ግን በጉልበት ሳይሆን በቀስታ፣ ጥጉን ይዞ በመግባቱ ጥፋቱን የሚያቀል ሳይመስለው አልቀረም። ከገባም በኋላ መንገዱን ለመልቀቅ እና ለማሳለፍ ብዙም ሲጣደፍ አይታይም። ይህ አሽከርካሪ ፍጥነት እንድቀንስ፣ ረድፍ እንድለውጥ ስላስገደደኝ ቅድሚያ እየከለከልኝ ነው።