በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

በአደጋ ጊዜ፣ በእርጥብ መንገድ፣ ድንገት ለመቆም የሚያስፈለግ ርቀት

በእርጥብ መንገድ፣ የአደጋ መንስኤ ከተከሰትር አንስቶ፣ እንዲሁም የ 1 ሰከንድ የምላሽ ጊዜን አካትቶ ድንገት ለመቆም የሚያስፈልገንን ርቀት ለመገመት የፍጥነታችንን የ 10 ቤት ቁጥር በራሱ እናባዛ እና የውጤቱን ግማሽ መልሰን እንደምራለን። በዚህም መሠረት ከላይ በተንቀሳቃሽ ሰዕሉ ላይ የሚታየው መኪና በ 50 ኪሜትር/ሰዓት እየተጓዘ ሲሆን የፍጥነቱን የ 10 ቤት ቁጥር 5ን በራሱ በማባዛት (5x5) ቀጥሎም የውጤቱን የ25ን ግማሽ በመጨመር በጥቅሉ ወደ 37.5 ሜትር (የ 10 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  እንደሚያስፈልገው ለማወቅ እንችላለን። በእርጥብ መንገድ ለመቆም ተጨማሪ ርቀት ማስፈለጉን አንዘንጋ።

በ 60 ኪሜትር/ሰዓት እየተጓዘ ቢሆን ኖሮ 6x6=36 ሲደመር (36/2) በማድረግ በድንገት ለመቆም ወደ 54 ሜትር (የ 15 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  እንደሚያስፈልገው መገመት እንችላለን።

 

ይህን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?

የአደጋ መንስኤ ሲከሰት ከነበረን ፍጥነት አኳያ ለመቆም የሚያስፈልገን ርቀት ከዕይታችን የሚበልጥ ከሆነ አደጋውን ለማስቀረት አይቻለንም። ለምሳሌ በ 50 ኪሜትር/ሰዓት እያሽከረከርን ለመቆም ወደ 37.5 ሜትር (የ 10 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  የሚያስፈለገን ሆኖ ሳለ የሚታየን ግን እስከ 30 ሜትር (የ 8 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ብቻ ከሆነ አደጋው መድረሱ አይቀሬ ነው። ፍጥነታችን 40 ኪሜትር/ሰዓት ቢሆን ግን ለመቆም የሚያስፈልገን ርቀት ወደ 24 ሜትር (የ 7 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ዝቅ ስለሚል 30 ሜትር (የ 8 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ላይ ያየነው የአደጋ መንስኤ ላይ ሳንደርስ መቆም እንችላለን ማለት ነው።

 

ይህን በማወቃችን ምን ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን?

በምናሽከረክርበት በማንኛውም ወቅት ከፍጥነታችን በመነሳት ለመቆም የሚያስፈልገንን ርቀት ማስላትና ከዕይታችን ጋር ማነጻጸር አለብን። ርቀቱ ከዕይታችን የሚበልጥ ከሆነ ለአደጋ የተጋለጥን ነን፤ ወደ ተገቢው ፍጥነት መመለስ አለብን።