በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

አደገኛ የምሽት አነዳድ

በዚህ ምሳሌ ላይ እንደሚታየው አሽከርካሪው በደረቅ መንገድ በ50 ኪሜ/ሰዓት እየተጓዘ ሲሆን ድንገት ለመቆም የሚያስፈልገው ርቀት ደግሞ ወደ 25 ሜትር (የ 7 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  እንደሚሆን አይተናል። ዕይታው ግን ወደ 20 ሜትር (የ 5.5 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ብቻ ነው። ታዲያ ድንገት የአደጋ ሁኔታ ቢከሰት የአደጋውን መንሰዔ የሚያየው 20 ሜትር (የ 5.5 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ላይ ሆኖ ሳለ ለመቆም ግን ወደ 25 ሜትር (የ 7 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ነው የሚያስፈልገው። በዚህ ሁኔታ አደጋውን ለማስቀረት አይቻለውም ማለት ነው።

 

ይህን በማወቃችን ምን ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን?

በማንኛውም ወቅት ስናሽከረክር (በቀንም ይሁን በምሽት) የሚቀጥሉትን 2 ጥያቄዎች ለራሳችን መጠየቅ ግድ ይላል። የመጀመሪያው ጥያቄ - አሁን በያዝኩት ፍጥነት የአደጋ መንሰዔ ቢከሰት ድንገት ለመቆም ምን ያህል ርቀት ያስፈልገኛል? - የሚለው ሲሆን ካገኘነው መልስ በመነሳት ቀጣዩ ጥያቄ ደግሞ - ያን ያህል ርቀት በግልጽ ማየት እችላለሁ ወይ? - የሚለው ነው። ከላይ በምሳሌ ከጠቀስነው ሁኔታ በመነሳት መልሱ - አይታየኝም - በመሆኑ አደጋው የመከሰቱ እድል ከፍተኛ ነው። በመሆኑም ፍጥነታችንን ከዕይታችን ጋር ለማጣጣም ዝግ ማለት አለብን ማለት ነው።
ማሳሰቢያ
  • በአገራችን በሚገኙ በቂ መብራት በሌላቸው መንገዶች፣ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጡ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በምሽት ስናሽከረክር እይታችን በጣም የተገደብ መሆኑን - ምናልባትም 20 ሜትር (የ 5.5 ቶዮታ ቪትዝ ርዝመት)  ላይደርስ እንደሚችል - መገንዘብ ያስፈልጋል።
  • የዕይታ መገደብን ለማሳየት በዚህ ገጽ ላይ የምሽት አነዳድን እንደምሳሌ ተጠቀምን እንጂ፣ በቀንም ቢሆን የመንገዱ አቀማመጥ፣ የሌሎች ተሽከርካሪዎች መኖር ወዘተ... እይታችን እጅጉን የተገደበ እንዲሆን ሊያደርጉ ይችላሉ።