በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

በውስጥና በውጪ መስታወቶች ለማየት ስንሞክር ከእይታ ውጪ ስለሆኑ አካባቢዎች

የቀዩ መኪና አሽከርካሪ በውስጥና በውጪ መስታወቶች ሲመለከት፣ በጥቁር የተመለከቱት አካባቢዎች ከዕይታው ውጪ ናቸው። በመሆኑም ሁለቱ ሰማያዊ መኪናዎች በፍጹም አይታዩትም።

ይህ አሽከርካሪ ረድፍ መለወጥ ሲፈልግ፣ በውስጥና በውጪ መስታወቶች ከማየት በተጨማሪ ጭንቅላቱን ለአፍታ በትከሻው ላይ ዞር በማድረግ የሚገባበት ረድፍ ውስጥ ሌላ ተሽከርካሪ አለመኖሩን ማረጋገጥ አለበት።

በሌላ በኩል ደግሞ፣ የሁለቱ ሰማያዊ መኪና አሽከርካሪዎች በእነዚህ ከዕይታ ውጪ በሆኑ አካባቢዎች ረዘም ላለ ጊዜ መቆየት የለባቸውም። የቀኙ መኪና ወደኋላ ቀረት በማለት፤ የግራው ደግሞ ፈጠን ብሎ በመቅደም ከማይታዩበት ቦታ መውጣት አለባቸው።

በተመሳሳይ፣ ለአንድ የከባድ መኪና አሽከርካሪ በዙሪያው ሰፋ ያሉ ከዕይታ ውጪ የሆኑ አካባቢዎች አሉ። ይህንን በመገንዘብ ሌሎች አሽከርካሪዎች ከነዚህ ከማይታዩ ቦታዎች መራቅ አለብን። የከባድ መኪናው አሽከርካሪ እንደሚያየን ወይም እንደማያየን ለማወቅ፣ የከባድ መኪናውን አሽከርካሪ በውጪ መስታወቶቹ ለመመልከት እንሞክር። ካየነው እሱም መልሶ ሊያየን ይችላል ማለት ነው፤ ልናየው ካልቻልን ግን እሱም ሊያየን አይችልም እና ቶሎ መራቅ አለብን።