በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

የሞተር ብስክሌት አደጋ ፤ የመንገድ ላይ ጉድጓድ

ይህ አደጋ በትክክል እንዴት እንደደረሰ ለመናገር ቢያስቸግርም አንዳንድ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ሃሳቦችን ግን መሰንዘር ይቻላል፡፡

  • ሞተር ሳይክሉ ከሚኒባሱ አሽከርካሪ ዕይታ ውጪ በሆኑት አካባቢዎች ውስጥ ገብቶ ፣ የሚኒባሱ ሾፌር ሳያየው ድንገተኛ የእንቅስቃሴ ለውጥ አድርጎ ይሆን?
  • ሞተር ሳይክሉ ሚኒባሱን አላግባብ ተጠግቶ ለመቅደም ሲሞክር ከግምቱ ውጪ የሆነ ነገር ተፈጥሮ ሚኒባሱን ገጭቶ ይሆን?

ማንኛውም የመንገድ ተጠቃሚ (በተለይ ሞተር ሳይክሎች፣ ብስክሌቶች) በአቅርራቢያቸው ያሉ ሌሎች አሽከርካሪዎች ላያይዋቸው እንደሚችሉ ተገንዝበው (ከዕይታ ውጪ ያሉ አካባቢዎች) የራሳቸውን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡