በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

የማይጠበቀው የተቃራኒ አቅጣጫ ጉዞ

ህግን በመተላለፍ በተቃራኒ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ለከፋ አደጋ ያጋልጣል። ይህም የሚሆንበት ምክንያት ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ከሚጠብቁት/ከሚገምቱት ውጪ የሆነ እንቅስቃሴ በመሆኑ ድንገተኛና ለመከላከል አዳጋች ስለሚሆን ነው። ይህ የማይጠበቅ እንቅስቃሴ በብስክሌቶች፣ ሞተር ብስክሌቶች ወይም በእግረኞች ሲፈጸም ደግሞ ጉዳቱ እጅግ የከፋ ይሆናል።

በዚህ ቪዲዮ የምትመለከቱት አሽከርካሪው ከመጋቢ መንገድ እየወጣ ወደ ዋና መንገድ ለመግባት እየተንቀሳቀሰ ነው። ቅድሚያ ያላቸውን መኪናዎች አሳልፎ ወደ ዋናው መንገድ በሚዞርበት ወቅት ድንገት በተቃራኒ አቅጣጫ ብስክሌተኛ ይመጣል። ባለመኪናው፣ ከሰከንድ በፊት ያላየው፣ ስለሆነም ያልገመተው ክስተት መሆኑን መሪው ላይ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ማስተዋል ይቻላል።

ብስክሌተኛው ወደ መጋቢው መንገድ በመዞሩ አደጋ አልተከሰተም። ግን ደግሞ ቀትታ ለመሄድ ተንቀሳቅሶ ቢሆን ኖሮ የከፋ ሁኔታ ሊፈጠር ይችል ነበር።

አሽከርካሪዎችም ከሰከንዶች በፊት የአደጋ ምክንያት አለመኖሩን አይተው ቢሆንም እንኳን፣ በእንዲህ ያለ ሁኔታ እንቅስቃሴያቸውን ከመቀጠላቸው በፊት ዳግም ማረጋገጥ ይገባቸዋል።

ከጥቂት ዓመታት በፊት፣ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አንድ አሽከርካሪ ትኩረቱን ቅድሚያ ወዳላቸውና በዋናው መንገድ ለሚያልፉ መኪናዎች አድርጎ በሚዞርበት ወቅት በተቃራኒ አቅጣጫ፣ በፍጥነት የሚመጣ ሞተር ብስክሌተኛ ገብቶበት አደጋ ተከስቷል። በመሆኑም ከላይ የተጻፈው ምናልባታዊ ሁኔታ ቢሆንም፣ በሌላ አጋጣሚ ሁኔታው በተግባር የተገለጸ ዓደጋ ምንጭ ሲሆን ተስተውሏል።

 

ተመሳሳይ ቪዲዮዎች