በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

ከባቢያዊ ግንዛቤ አለመያዝ

በምናሽከረክርበት ወቅት ቀጣይነት ባለው መልኩ ከባቢያችን ላይ ምን እየሆነ እንዳለ ግንዛቤ መያዝ አለብን።

ከኋላችን፣ በቀኝ በኩል፣ በግራ በኩል ምን ኣይነት ተሽከርካሪ አለ? ፍጥነቱ፣ ርቀቱ ምን ይመስላል? ከፊታችን ምን ዓይነት ሁኔታ ይጠብቀናል? የሚልሉትን እና መሰል ጥያቄዎችን በማገናዘብ እንቅስቃሴያችንን ማስተካከል አለብን።

ከፊት የምትመለከቱት ቀይ ቶይታ አሽከርካሪ ከባቢያዊ ግንዛቤ ቢኖረው ኖሮ ከኋላው እየቀረበው መጥቶ ለማለፍ የሚሞክር ተሽከርካሪ እንዳለ ተረድቶ ወደ ቀኙ ረድፍ በመግባት መንገድ ይለቅ ነበር፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ከአንዴም ሁለቴ ጥሩምባ ተደርጎለት ነው መንገድ የሚለቀው።

እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች፣ ለመቅደም የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች ወዲህ ወዲያ እያሉ ረድፍ በመቀያየር ለማለፍ እንዲሞክሩ ያስገድዷቸዋል። ረድፍ መቀያየር ደግሞ የራሱ አደጋ እንዳለው በሌላ ቪዲዮ ተመልክተናል።