በግንዛቤ ላይ ተመስርተው በሠላም ይድረሱ!

ማስታወቂያ

በሃገራችን የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም በሰው እና በንብረት ላይ የሚያደርሱት የአደጋ መጠን ግን እጅግ ከፍተኛ ነው።

ይህ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ መስተካከል ካላመራ እየተስተዋለ ባለው የመንገዶች እና የእንቅስቃሴ መስፋፋት ምክንያት ጉዳቱ እየገዘፈ መሄዱ የማይቀር ነው።

"በፍጥነት፤ ርቀት እና ዕይታ ተያያዥነት
ላይ የሚስተዋለው የግንዛቤ ማነስ የችገሩ
ዋነኛ መንሰዔ ነው"

የዚህ ሥራ አላማም የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት ማገዝ ሲሆን የሚያተኩረውም በፍጥነት፤ ርቀት እና ዕይታ ላይ ነው። በአዘጋጁ እምነት በፍጥነት፤ ርቀት እና ዕይታ ተያያዥነት ላይ የሚስተዋለው የግንዛቤ ማነስ የችገሩ ዋነኛ መንሰዔ ነው። በመሆኑም አደጋን ተከላክሎ ለማሽከርከር ይራዳሉ ተብለው የሚታመንባቸውን ምክሮች እና ስሌቶች ለማካተት ተሞክሯል። ስሌቶቹ በማንኛውም አሽከርካሪ በቀላሉ ሊሰሩ የሚችሉ ሲሆን ከእውነታው ጋር ተቀራራቢ ውጤት እና ጠቋሚ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ናቸው። (ጠቋሚ የተሰኘበት ምክንያት እንደ ተሽከርካሪው ይዞታ፤ እንደ አሽከርካሪው ሁኔታ፤ እንደ ከባቢያዊ ሁኔታዎች፤ ውጤቶቹ ተለዋዋጭ ስለሚሆኑ ነው።)

ይህን ሥራ በተገቢው ለመጠቀም መሠረታዊ እውቀቶች በተሰኘው ገጽ ላይ የሚገኙትን አኒሜሽኖች በቅደም ተከተል በመክፈት መመልከት እና በግርጌአቸው ቀጣዩን ገጽ የሚጠቁሙ ከሆነ እሱን ተከትሎ መቀጥል። ተያያዥ ገጾች ከዳር ሲደርሱ ወደ መሠረታዊ እውቀቶች ገጽ በመመለስ በተመሳሳይ መልኩ ፍሰቱ መከተል ይገባል።

ርዝመቶችን/ርቀቶችን በተሻለ ለማስገንዘብ ይቻል ዘንድ ከትንሾቹ ቶዮታ ቪትዝ መኪናዎች ርዝመት ጋር በንጽጽር ለማስቀመጥ ተሞክሯል። ለዚህም ቁጥሮቹ ላይ ይጠቁሙ።

በዚህ ሥራ ውስጥ የተካተቱት ጭብጦች፣ ከችግሩ አሳሳቢነት አኳያ በቅድሚያ የተዘጋጁ ይሁን እንጂ በቀጣይ ሌሎች የሚከተሉ ይሆናል። ተደራሽነታቸውም በሥልጠና ላይ ለሚገኙ የወደፊት አሽከርካሪዎች (ከመደበኛው ትምህርት በተጨማሪ)፤ እንዲሁም ለነባር አሽከርካሪዎች ሲሆን ሁሉንም ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሎ ይታመናል።